Luke 14:3-6

Amharic(i) 3 ኢየሱስም መልሶ። በሰንበት መፈወስ ተፈቅዶአልን ወይስ አልተፈቀደም? ብሎ ለሕግ አዋቂዎችና ለፈሪሳውያን ተናገረ። 4 እነርሱ ግን ዝም አሉ። ይዞም ፈወሰውና አሰናበተው። 5 ከእናንተ አህያው ወይስ በሬው በጕድጓድ ቢወድቅ በሰንበት ወዲያው የማያወጣው ማን ነው? አላቸው። 6 ስለዚህ ነገርም ሊመልሱለት አልተቻላቸውም።