Amharic(i)
7 ፋሲካንም ሊያርዱበት የሚገባው የቂጣ በዓል ደረሰ፤ 8 ጴጥሮስንና ዮሐንስንም። ፋሲካን እንድንበላ ሄዳችሁ አዘጋጁልን ብሎ ላካቸው። 9 እነርሱም። ወዴት እናዘጋጅ ዘንድ ትወዳለህ? አሉት። 10 እርሱም አላቸው። እነሆ፥ ወደ ከተማ ስትገቡ ማድጋ ውኃ የተሸከመ ሰው ይገናኛችኋል፤ ወደ ሚገባበት ቤት ተከተሉት፤ 11 ለባለቤቱም። መምህሩ። ከደቀ መዛሙርቴ ጋር ፋሲካን የምበላበት የእንግዳ ቤት ክፍል ወዴት ነው? ይልሃል በሉት፤ 12 ያም በደርብ ላይ ያለውን የተነጠፈ ታላቅ አዳራሽ ያሳያችኋል፤ በዚያም አሰናዱልን። 13 ሄደውም እንዳላቸው አገኙና ፋሲካን አሰናዱ።