Matthew 24:17-21

Amharic(i) 17 በሰገነትም ያለ በቤቱ ያለውን ሊወስድ አይውረድ፥ 18 በእርሻም ያለ ልብሱን ይወስድ ዘንድ ወደ ኋላው አይመለስ። 19 በዚያችም ወራት ለርጉዞችና ለሚያጠቡ ወዮላቸው። 20 ነገር ግን ሽሽታችሁ በክረምት ወይም በሰንበት እንዳይሆን ጸልዩ፤ 21 በዚያን ጊዜ ከዓለም መጀመሪያ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ያልሆነ እንግዲህም ከቶ የማይሆን ታላቅ መከራ ይሆናልና።