Galatians 5:22-26

Amharic(i) 22 የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ ትዕግሥት፥ ቸርነት፥ በጎነት፥ እምነት፥ የውሃት፥ ራስን መግዛት ነው። 23 እንደዚህ ያሉትን የሚከለክል ሕግ የለም። 24 የክርስቶስ ኢየሱስም የሆኑቱ ሥጋን ከክፉ መሻቱና ከምኞቱ ጋር ሰቀሉ። 25 በመንፈስ ብንኖር በመንፈስ ደግሞ እንመላለስ። 26 እርስ በርሳችን እየተነሣሣንና እየተቀናናን በከንቱ አንመካ።