Romans 10:11-14

Amharic(i) 11 መጽሐፍ። በእርሱ የሚያምን ሁሉ አያፍርም ይላልና። 12 በአይሁዳዊና በግሪክ ሰው መካከል ልዩነት የለምና፤ አንዱ ጌታ የሁሉ ጌታ ነውና፥ ለሚጠሩትም ሁሉ ባለ ጠጋ ነው፤ 13 የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናልና። 14 እንግዲህ ያላመኑበትን እንዴት አድርገው ይጠሩታል? ባልሰሙትስ እንዴት ያምናሉ? ያለ ሰባኪስ እንዴት ይሰማሉ?