John 6:47-50

Amharic(i) 47 እውነት እውነት እላችኋለሁ በእኔ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው። 48 የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ። 49 አባቶቻችሁ በምድረ በዳ መና በሉ ሞቱም፤ 50 ሰው ከእርሱ በልቶ እንዳይሞት ከሰማይ አሁን የወረደ እንጀራ ይህ ነው።