Amharic(i) 1 እንዳትሰናከሉ ይህን ተናግሬአችኋለሁ። 2 ከምኵራባቸው ያወጡአችኋል፤ ከዚህ በላይ ደግሞ የሚገድላችሁ ሁሉ እግዚአብሔርን እንደሚያገለግል የሚመስልበት ጊዜ ይመጣል።