Hebrews 7:7 Cross References - Amharic

7 ትንሹም በታላቁ እንዲባረክ ክርክር የሌለበት ነገር ነው።

Luke 24:50-51

50 እስከ ቢታንያም አወጣቸው እጆቹንም አንሥቶ ባረካቸው።51 ሲባርካቸውም ከእነርሱ ተለየ ወደ ሰማይም ዐረገ።

2 Corinthians 13:14

14 የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ የእግዚአብሔርም ፍቅር የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን። አሜን።

1 Timothy 3:16

16 እግዚአብሔርንም የመምሰል ምሥጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው፤ በሥጋ የተገለጠ፥ በመንፈስ የጸደቀ፥ ለመላእክት የታየ፥ በአሕዛብ የተሰበከ፥ በዓለም የታመነ፥ በክብር ያረገ።

Hebrews 11:20-21

20 ይስሐቅ ሊመጣ ስላለው ነገር ያዕቆብንና ዔሳውን በእምነት ባረካቸው።21 ያዕቆብ ሲሞት በእምነት የዮሴፍን ልጆች እያንዳንዳቸው ባረካቸው፥ በዘንጉም ጫፍ ተጠግቶ ሰገደ።

Cross Reference data is from OpenBible.info, retrieved June 28, 2010, and licensed under a Creative Commons Attribution License.