Matthew 12:18-21

Amharic(i) 18 እነሆ የመረጥሁት ብላቴናዬ፥ ነፍሴ ደስ የተሰኘችበት ወዳጄ፤ መንፈሴን በእርሱ ላይ አኖራለሁ፥ ፍርድንም ለአሕዛብ ያወራል። 19 አይከራከርም አይጮህምም፥ ድምፁንም በአደባባይ የሚሰማ የለም። 20 ፍርድን ድል ለመንሣት እስኪያወጣ፥ የተቀጠቀጠን ሸምበቆ አይሰብርም የሚጤስን የጥዋፍ ክርም አያጠፋም። 21 አሕዛብም በስሙ ተስፋ ያደርጋሉ።