Luke 24:49-53

Amharic(i) 49 እነሆም፥ አባቴ የሰጠውን ተስፋ እኔ እልክላችኋለሁ፤ እናንተ ግን ከላይ ኃይል እስክትለብሱ ድረስ በኢየሩሳሌም ከተማ ቆዩ። 50 እስከ ቢታንያም አወጣቸው እጆቹንም አንሥቶ ባረካቸው። 51 ሲባርካቸውም ከእነርሱ ተለየ ወደ ሰማይም ዐረገ። 52 እነርሱም፤ ሰገዱለትና በብዙ ደስታ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ፥ 53 ዘወትርም እግዚአብሔርን እያመሰገኑና እየባረኩ በመቅደስ ኖሩ።