John 17:17-19

Amharic(i) 17 በእውነትህ ቀድሳቸው፤ ቃልህ እውነት ነው። 18 ወደ ዓለም እንደ ላክኸኝ እንዲሁ እኔ ወደ ዓለም ላክኋቸው፤ 19 እነርሱም ደግሞ በእውነት የተቀደሱ እንዲሆኑ እኔ ራሴን ስለ እነርሱ እቀድሳለሁ።