Luke 22:55-57

Amharic(i) 55 በግቢ መካከልም እሳት አንድደው በአንድነት ተቀምጠው ሳሉ ጴጥሮስ በመካከላቸው ተቀመጠ። 56 በብርሃኑም በኩል ተቀምጦ ሳለ አንዲት ገረድ አየችውና ትኵር ብላ። ይህ ደግሞ ከእርሱ ጋር ነበረ አለች። 57 እርሱ ግን። አንቺ ሴት፥ አላውቀውም ብሎ ካደ።